እንኳን ደስ አላችሁ አለን!
የላንፉሮ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት 2ኛ ደረጃን በመያዝ የኮምፒውተርና የምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆነ!
**********************************
ጦራ/ሐምሌ 9/2018 ዓ.ም./ላንፉሮ ኮሙኒኬሽን/ቅ/ጽ/ቤቱ የተሸለመው"ከምርጫ ማግስት ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ መንግሥት"በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት የስልጤ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ባዘጋጀው የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም የማጠቃለያ መድረክ በዞኑ ዓለም ገበያ ከተማ ላይ ባካሄደው መድረክ ነው።
የላንፉሮ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተሻሉ ስራዎችን በማከናወን ነው በስልጤ ዞን ካሉ አጠቃላይ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤቶች የተሻለ አፈጻጸምን በማስመዝገብ 2ኛ ደረጃን ይዞ ኮምፒውተር ከነ ሙሉ አክሰሰሪውና የምስክር ወረቀት የተሸለመው።
ጽ/ቤቱ ያስመዘገበው የተሻለ ውጤት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ድምር ውጤት መሆኑን የገለጹት የላንፉሮ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሴ ሳዲቅ ለዚህ ውጤት እና ሽልማት መገኘት የበኩላቸውን የተወጡ አካላትን በሙሉ አመስግነዋል።
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ አለን!