የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ በላንፉሮ ወረዳ እየተከናወኑ የሚገኙ የግብርና ልማት ስራዎች ላይ ምልከታ አደረጉ!
ጦራ/መስከረም 2/2019 ዓ.ም.ላንፉሮ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን/የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ፣ የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሙበራ ከማል እንዲሁም የላንፉሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሸምሴ ጉንዳ፣ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሸምሴ ሳዲቅ እና የወረዳው ምክትል አስተዳደሪና ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብደላ አህመድ በወረዳው ቁዱሳ ቀበሌ ላይ ተገኝተው የዶሮ መንደርንና የቡናና ፍራፍሬ ልማት ስራዎች ላይ ምልከታ አድርገዋል፡፡
በወረዳው የተጀመረው የተቀናጀ የግብርና ልማት ስራዎችን የማስፋፋት ስራ በመስራት አርሶ አደሮችን የበለጠ ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባም አቶ ዘይኔ ገልጸዋል፡፡